በመንግስት ተቋማት የመንግስት ሰራተኞች የወቅታዊ ኩነት ምዝገባን አስመልክቶ ግንዛቤ ተሰጠ

ታህሳስ 1, 2017
በል/ክ/ከተማ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ግንዛቤ የተሰጠው ተመሳሳይነት ያለው እውቀት ኖሯቸው ተግባራቱ በብቃት በጥራትና በወቅቱ ኩነትን እንዲያስመዘግብ ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ መቅደስ እንደገለፁት የመንግስት የሠራተኞች እረፍት በሚወጡበት ጊዜ የሚያጋጥማቸውን ኩነት ማለትም ልደት፣ሞት፣ጋብቻ፣ፍች፣ጉድፈቻን በወቅቱና በስዓቱ ማስመዝገብ እንደሚገባ በመግለፅ ኩነት ማስመዝገብ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት ሲሉ ገልፀዋል። ሀላፊዋ አክለው ጽ/ቤቱ በቀጣይም ወጥነት ያለው ስራዎችን ለመስራት የሰው ሀብት ልማት የተመዘገበ ኩነቶችን ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባውና ሰራተኞች ወጥነትና ተመሳሳይነት ያለው ግንዛቤ በመስጠት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረን ይጠቅማል በማለት ገልፀዋል። ተሳታፊዎችም የተሰጠው ግንዛቤ የተሻለ ሲሆን በቀጣይ ሁሉም አካል ኩነት ማስመዝገብ ላይ ግንዛቤ ኖሮት በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለበት ገልጿል።

© 2025 Lideta Civil Registration and Residency Servic. Designed by  Markos MG 0912689710.