`

የዜጎች የስምምነት ሰነድ |
Citizens Charter

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የከተማውን የአስፈጻሚ አካላት እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 79/2015 ዓ.ም መሰረት የከተማውን ነዋሪዎች የመመዝገብ እና በከተማው የሚከሰቱትን ኩነት በመመዝገብ፣ ማስረጃ በመስጠት በማደራጀትና በመተንተን ለሚመለከተው የፌደራር አካል ለህግ፣ ለአስተዳደርና ለስታቲስቲክስ የመረጃ ምንጭነት እንዲውል በሚያስችል መልኩ አደራጅቶ የማስተላለፍ ስልጣን ያለው ሲሆን ይህን የወሳኝ ኩነት ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ተግባራት በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ይሰራል፣ ያስተባብራል እንዲሁም ይቆጣጠራል፡፡

በመሆኑም ኤጀንሲው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና የብሔራዊ መታወቂያ አዋጅ 760/2004 ዓ.ም እና በተሻሻለው አዋጅ 1049/2009 ዓ.ም እንዲሁም የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ ማሻሻያ አዋጅ 84/2016 በተጨማሪም በነዋሪነት አገልግሎት መመሪያ ቁጥር 145/2015 መሰረት በማድረግ ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞት፣ አባትነትን በፍርድ ቤት መቀበል፣ ልጅነትን በፍርድ ቤት መቀበል እንዲሁም የነዋሪነት አገልግሎቶችን ማለትም የነዋሪነት መታወቂያ፣ ያላገባ፣ የነዋሪነት፣ መሸኛ፣ የነዋሪነት ማረጋገጫ፣ በህይወት ስለመኖር፣ ለማህበራዊ ዋስትና የእናትነት፣ የአባትነት፣የልጅነት እህትነት፣ ወንድምነትና አያትነት ከቅጽላይ በማየት የማረጋገጥ እና ለማህበራዊ ዋስትና ብቻ ያላገባ ማስረጃ በደብዳቤ የመስጠት አገልግሎቶች ይሰጣሉ፡፡ በመሆኑም ተቋሙ አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆኑ መጠን የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮን ከግብ ለማድረስ ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር ስርዓት በመዘርጋትለዜጎች አገልግሎቶች የሚሰጥባቸውን ቦታ፣ የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታና ደጋፊ ማስረጃዎች ስታንዳርድ(ጊዜና ጥራት) በግልጽ በማስቀመጥ በተቋሙ እና በዜጎች መካከል ባለው የአሰራር ሂደት ላይ መብትና ግዴታቸውን እንዲረዱ እና የአገልግሎት አሰጣጡን ፈጣንና ቀልጣፋ በማድረግ የዜጎችን የእርካታ ደረጃ ከፍ ማድረግ ያስችላል፡፡

የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ

  1. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በዝርዝር ዜጎች እንዲያውቁት በማድረግ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር በመዘርጋት፤ ብልሹ አሰራር እና ተግባራት በማስወገድ፤ መልካም አስተዳደር የሰፈነበት በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ እና ውጤታማእንዲሁም የላቀ ውጤት ማምጣት ነው፡፡

የዜጐች የስምምነት ሰነድ አስፈላጊነት

  1. ተገልጋዮችን/customers/ እና ባለድርሻ አካላት /stakeholders/ ፍላጎቶችን መሰረት በማድረግ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፤
  2. የዜጎችን የመረጃ ማግኘት መብት ለማረጋገጥና በጽ/ቤቱ የሚሰጡትን አገልግሎቶች በምን ዓይነት ደረጃ/standard/ ማግኘት እንደሚገባቸው ለማሳወቅ
  3. ፈጣን ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራር ስርዓትን በመዘርጋት ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት በቂ የሆነ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ለማድረግ እና
  4. የተገልጋዮችን እንግልት በመቀነስ የአገልግሎት እርካታውን እንዲጨምር ለማድረግ ነው፡፡

የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

  1. በከተማ አስተዳደሩ የወሳኝ ኩነት ምዝገባን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤ ይመዘግባል፤ መመዝገቡንም ይቆጣጠራል ይከታተላል
  2. የነዋሪዎች መታወቂያና ሌሎችንም አገልግሎቶቸ ይሰጣል
  3. የክብር መዝገቦች ዝግጅትና ስርጭትን መረጃ አጠቃቀም ስርዒት አግባብ ካለው የፌደራል አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል፤ ድጋፍ ይሰጣል፤ የክብር መዝገቦች ለሁሉም ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ደህንነት ጽ/ቤቶች መሰራጨታቸውን ያረጋግጣል፡፡
  4. የፈወሳኝ ኩነት ምዝገባ አስፈላጊነትን አስመልክቶ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ግንዛቤ ይፈጥራል ወይም እንዲፈጠር ያደርጋል፤
  5. የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የጥራትና የሽፋን ደረጃ ለመገምገምና ለመቆጣጠር የሚያስችል ጥናት ያካሂዳል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤
  6. የወሳኝ ኩነት ምዝገባና ብሔራዊ መታወቂያ አዋጅ መሰረት የተሰበሰቡ መረጃዎችን አግነባብ ላለው ለፌደራል አካላት በወቅቱ ያስተላልፋል፤
  7. በቴክኖሎጂ በመታገዝ የዲሞክራሲና የባዮሜትሪክ የሰዎችን መረጃ ይመዘግባል፤ አገልግሎት ይሰጣል፤ ያስተዳደርራል፤ ይቆጣጠራል፤
  8. መንግስታዊ ተቋማት ማህበራትና የበጎ አድራጊዎች ድርጅቶች የሚደረገው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓት የተሟላ እንዲሆን ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ያስተባብራል፤
  9. የድጂታል አገልግሎትን በከተማዋ በማሳለጥ የግለሰብ መረጃ መብትን በጠበቀ መልኩ የተመዝጋቢዎችን መረጃ እንደ አስፈላጊነቱ ለተቋማት ያጋራል፣ ደህንነቱንም ያስጠብቃል ወይም ይቆጣጠራል፤

ራዕይ/Vision/

  • በ2022 ዓ.ም የወሳኝ ኩነት እና የነዋሪዎች ምዝገባ አገልግሎቶች በማዘመን ዋነኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ማየት፡፡

ተልዕኮ/Mission/

  • አገልግሎቶችን በማዘመን፤ በወሳኝ ኩነት መርሆችን መሰረት የሚከሰቱ ኩነቶችን እና ነዋሪዎች መመዝገብና አገልግሎት ቀልጣፋ እና ተደራሽ ማድረገ

እሴቶች/Core Values)

  • አገልጋይነት
  • ስነ-መግበራ
  • ግልፅነትና ተጠያቂነት
  • በቡድን መስራት
  • የመረጃ ደህንነትና ሚስራዊነት መጠበቅ
  • ለለውጥ ዝግጁ መሆን

ስትራቴጂካዊ የትኩረት መስኮችና ውጤቶች

ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች

  1. የላቀ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ፣ መረጃና ማስረጃ መስጠት፤
  2. የላቀ የነዋሪዎች ምዝገባ እና አገልግሎት መስጠት፤
  3. የላቀ የወሳኝ ኩነትና የነዋሪዎች ምዝገባና መረጃ አገልግሎት ማዘመን፤

ስትራቴጂያዊ ውጤቶች

  1. የሚከሰጡ የወሳኝ ኩነቶችን በመመዝገብ የምዝገባ መረጃ ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ማድረግ
  2. ከነዋሪዎች ምዝገባ የተገኙ መረጃዎች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ማስቻል
  3. የወሳኝ ኩነት እና የነዋሪዎች ምዝገባ፣ መረጃና ማስረጃ አገልግሎትን በማዘመን ጥራት ያለው፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ማድረግ

የተገልጋዮች መብት

  1. የምክር አገልግሎት የማግኘት
  2. ተገልጋዮች በሚኖሩበት ክፍለ ከተማና ወረዳዎች አገልግሎቶችን የማግኘት
  3. በተቋሙ ውስጥ ስለሚሰጡ አገልግሎቶች ሙሉ መረጃ የማግኘት
  4. ለሚፈጠሩ ቅሬታዎች ምላሽ የማግኘት
  5. ጥራቱ የተወሰነ ፍትኃዊና አድሎ የሌለበት አገልግሎት የማግኘት
  6. በተቀመጠው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት የመስተናገድ

የተገልጋዮች ግዴታዎች

  1. በተቋሙ አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ ትክክለኛ መረጃዎችን የማግኘት
  2. የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላትና የማቅረብ
  3. የተቋሙን ህግና ስርዓት የማክበር

የተቋሙ ግዴታ

  1. በተቋሙ ውስጥ በሚሰጡ አገልግሎቶች ዙሪያ ተገልጋዩን ህብረተሰብ የማሳተፍ
  2. በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አገልግሎት መስጠት
  3. በተቋሙ ለሚሰጡ አገልግሎቶች የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን የማሳወቅ
  4. ለተገልጋዩ ህብረተሰብ የምክር አገልግሎት የመስጠት
  5. ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ስለ አገልግሎት ሙሉ መረጃ መስጠት
  6. ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ለሚፈጥሩ ቅሬታዎች ምላሽ የመስጠት
  7. ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ፍትሃዊ፣ አድሎ የሌለበት አገልግሎት የመስጠት እና በእኩልነት የማገልገል
  8. በየጊዜው የተገልጋዩን እርካታ ያለበትን ደረጃ የመጠየቅ
  9. ዜጎች በተቋሙ ምዘና እንዲሳተፉ የማድረግ
  10. የተቋሙን ህግና ደንብ የማሳወቅ
  11. አገልግሎቱን ለማቅረብ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን የማሟላት
    የተቋሙን የዜጎች የስምምነት ሰነድ pdf መረጃ ከፈለጉ ከፈለጉ ይህን Citizens Charter ይጫኑ