ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የልደታ ክ/ከተማ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ገለጸ።

ህዳር 24, 2017
ጽ/ቤቱ ከተለያዩ ጽ/ቤቶች ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን ገምግሟል ። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ መቅደስ ያደታ እንደገለጹት ከተለያዩ ጽ/ቤቶች ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር በጋራ በመስራት የተቋሙን ሰፊ ስራዎች ቀልጣፋ እንዲሆን ስለሚረዳ በትስስር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። ኃላፊዋ አክለውም በተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ውጤታማ ስራ ለመስጠት በቅንጅትና በትስስር መስራት አስፈላጊ በመሆኑ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

© 2025 Lideta Civil Registration and Residency Servic. Designed by  Markos MG 0912689710.