- በከተማ አስተዳደሩ የወሳኝ ኩነት ምዝገባን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤ ይመዘግባል፤ መመዝገቡንም ይቆጣጠራል ይከታተላል
- የነዋሪዎች መታወቂያና ሌሎችንም አገልግሎቶቸ ይሰጣል
- የክብር መዝገቦች ዝግጅትና ስርጭትን መረጃ አጠቃቀም ስርዒት አግባብ ካለው የፌደራል አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል፤ ድጋፍ ይሰጣል፤ የክብር መዝገቦች ለሁሉም ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ደህንነት ጽ/ቤቶች መሰራጨታቸውን ያረጋግጣል፡፡
- የፈወሳኝ ኩነት ምዝገባ አስፈላጊነትን አስመልክቶ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ግንዛቤ ይፈጥራል ወይም እንዲፈጠር ያደርጋል፤
- የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የጥራትና የሽፋን ደረጃ ለመገምገምና ለመቆጣጠር የሚያስችል ጥናት ያካሂዳል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የወሳኝ ኩነት ምዝገባና ብሔራዊ መታወቂያ አዋጅ መሰረት የተሰበሰቡ መረጃዎችን አግነባብ ላለው ለፌደራል አካላት በወቅቱ ያስተላልፋል፤
- በቴክኖሎጂ በመታገዝ የዲሞክራሲና የባዮሜትሪክ የሰዎችን መረጃ ይመዘግባል፤ አገልግሎት ይሰጣል፤ ያስተዳደርራል፤ ይቆጣጠራል፤
- መንግስታዊ ተቋማት ማህበራትና የበጎ አድራጊዎች ድርጅቶች የሚደረገው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓት የተሟላ እንዲሆን ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ያስተባብራል፤
- የድጂታል አገልግሎትን በከተማዋ በማሳለጥ የግለሰብ መረጃ መብትን በጠበቀ መልኩ የተመዝጋቢዎችን መረጃ እንደ አስፈላጊነቱ ለተቋማት ያጋራል፣ ደህንነቱንም ያስጠብቃል ወይም ይቆጣጠራል፤