image
image
image
image
image

የወሳኝ ኩነት ምዝገባን በወቅቱ በማስመዝገብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸዉን እንዲያረጋግጡ ለ300 ለሴቶች ስልጠና ተሰጠ።

ታህሳስ 18, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ መቅደስ ያደታ እንደተናገሩት ሴቶች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ተጠቃሚነታቸዉን ለማረጋገጥ የወቅታዊ ኩነት ምዝገባ ወሳኝ መሰረት መሆኑን በመግለፅ የሚወለድ ህፃናት በወቅቱ የልደት ካርድ እዲያወጡ በማስቻል የህፃኑን ማንነት እዲረጋገጥ በማድረግ ሴቶች ማህበራዊ ግዴታችሁን መወጣት ይገባችኋል በማለት ገልፀዋል። ወ/ሮ መቅደስ አያይዘው ሴቶችን ማብቃት ሀገራዊ እድገትን ያሳልጣል፣ ሴትን ማብቃት ሀገርን ትውልድን ማነፅ በመሆኑ ሴቶች በማስተማር ያላቸውን ሚና ማሳደግ ያስፈልጋል በማለት ሴቶች በጽ/ቤታችን እያደረጉ ያለው አስተዋፅኦ የሚበረታታ መሆኑን በመግለፅ ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሲሉ ተናግረዋል። ተሳታዎችም ሴቶችን ለማብቃት ታስቦ በዚህ ልክ መድረክ በማዘጋጀት ግንዛቤ መሰጠቱ የተሻለ ነው በማለት አንስተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች